
የዮናታን ጉዞ፡ ከባህሪይ ችግር እስከ ጥበባዊና ሙያዊ ስኬት
ዮናታን ተክሌ ሀይሌ
- ዕድሜ
- 23 ዓመት
- ፆታ
- ወንድ
- አካባቢ
- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ
- የድጋፍ መስክ
- የባህሪይ እና የሙያ ድጋፍ
ዮናታን፣ ቀደም ሲል ከባድ የባህሪይ ችግሮች እና የመማር ውስንነት የነበረበት፣ በራዕይ ሕፃናት መርጃ ድርጅት የስነ-ልቦና ድጋፍ፣ የባህሪይ ህክምና እና በሙዚቃና በሽመና የሙያ ስልጠና አማካኝነት ተለውጧል። አሁን የኪነ-ጥበብ ቡድን አባል የሆነ የኪቦርድ ተጫዋች እና የሽመና ሰራተኛ ሆኗል።
ከድጋፍ በፊት
በፊትከድርጅቱ ድጋፍ በፊት ዮናታን ከፍተኛ የባህሪ ችግር የነበረበት ሲሆን፣ የመማር ውስንነቱም ከሰዎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት እና በዕለት ተዕለት ህይወቱ ላይ ተደራራቢ እንቅፋት ፈጥሮበት ነበር። የባህሪ መታወክ፣ ስሜትን የመቆጣጠር ውስንነት እና ድጋፍ ማጣት ነበረበት።
የተሰጠ ድጋፍ
በራዕይ ሕፃናት መርጃ ድርጅት (RCA) ማዕከል የስነ-ልቦና ድጋፍ፣ የባህሪ ማሻሻያ እና ምክር (Behavioral Therapy)፣ የሙያ እና ሙዚቃ ክህሎት ሥልጠናዎች ተደርገዋል።
የተሳተፈባቸው ፕሮግራሞች
የባህሪ ማገገሚያ፣ የኪነ-ጥበብ እና የሙዚቃ (የኪቦርድ/Keyboard) ስልጠና፣ እና ባህላዊ የሽመና ሙያ ልማት።
የታዩ ለውጦች
በኋላበባህሪው ላይ ከፍተኛ እና አዎንታዊ ለውጥ ማሳየት፣ ስሜቱን በሙዚቃ እና የእጅ ጥበብ መግለጽ መቻሉ፣ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ራሱን መቆጣጠር እና ማህበራዊ ውህደት መፍጠር ችሏል።
ዋና ዋና ስኬቶች
የኪቦርድ (Keyboard) ተጫዋች ሙዚቀኛ በመሆን በራዕይ ሕፃናት መርጃ ድርጅት የኪነ-ጥበብ ቡድን ውስጥ ንቁ አባል መሆን ችሏል፤ በተጨማሪም በድርጅቱ ውስጥ በሽመና ሙያ የተቀጠረ ሰራተኛ ለመሆን በቅቷል።
ከማዕከሉ የተደረገለት የባህሪ ማሻሻያ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ዮናታን የነበረበትን ከባድ የባህሪ ችግር ተሻግሮ፣ በሙዚቃ እና በሽመና ስራ ድንቅ ብቃቱን እንዲያሳይ እና የድርጅቱ የኪነ-ጥበብ ቡድን አባልና ሰራተኛ እንዲሆን አስችሎታል።
ሌላ የለውጥ ጉዞ እንዲጀምር ያግዙ
ድጋፍዎ ራየ ችልድረን ኤይድ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ፣ ተግባራዊ ክህሎትና የእድገት ዕድሎችን እንዲያቀርብ ያግዛል።